የጥበብና የቴክኖሎጂ ውህደት.
· Other
Ethiopia’s One Million Birr AI Music Competition Nears Finale, Advancing Creative Innovation, Youth Talent, and Digital Economic Growth
የአንድ ሚሊዮን ብሩ የኤ.አይ ሙዚቃ ውድድር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሷል::
የፈጠራ ኢንዱስትሪን ወደ አዲስ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ለማሸጋገርየኢትዮጵያ አርቲፊሻልኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትከእሁድ ኤ.አይስቱዲዮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የኤ.አይየሙዚቃ ውድድር ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ተቃርቧል።
ለምንተዘጋጀ? ይህ ውድድር የሀገራችንን የጀግንነት ታሪክ በተለይም የዓድዋ ድልን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ታግዞ ለመዘከር የተዘጋጀ ነው፡፡ ወጣቱትውልድ ታሪኩን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አዛምዶ እንዲረዳ ትልቅ በርከፍቷል።
የሽልማቱፋይዳ፦ ውድድሩ የሚያስገኘው የ1 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት ብቻ ሳይሆን፤ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችናከያንያን ያላቸውን ክህሎት እንዲያሳድጉና
በዘርፉ አዳዲስ ግኝቶችን እንዲያበረክቱትልቅ እድል የከፈተ ሆኗል።
አሁንምን ደረጃላይ ይገኛል? 528 ተወዳዳሪዎች ስራዎቻቸውን አስገብተዋል፡፡ የህዝብ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት በስኬት ተጠናቋል። የዳኞች ቡድኑም ግምገማውን እያካሄደ ነው፡፡ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎችበቅርቡ በሚካሄድ ደማቅሥነ-ሥርዓት የሚታወቁበት እና ሽልማታቸውን የሚረከቡብት ሁነት በኢትዮጵያ አርቲፊሻልኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቅርቡ ይዘጋጃል፡፡ የኢትዮጵያንየፈጠራ አድማስ የሚያሰፋው ይህ ጉዞ ገናጅምሩ ነው!
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute