የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሥራ ጉብኝት አካሄዱ
· Visiting
Safaricom Ethiopia and EAII discussed collaboration to empower young talent and advance AI innovation.
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄሌፑት እና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እና የጋራ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ ከግሉ ዘርፍ ጋር በጥምረት ለመሥራት ሁልጊዜ በሩ ክፍት መሆኑን ጠቁመው ፤
ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመሥራት ያለውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄሌፑት በበኩላቸው በኢትዮጵያ በርካታ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች መኖራቸውን በጉብኝታቸው መታዘባቸውን ገልጸው፤ እነዚህን ወጣቶች ለማበቃትና ለመደገፍ ከኢንስቲትዩቱ ጋር መሥራት ወሳኝ መሆኑንና ኢንስቲትዩቱም ለዚህ ተስማሚ ቦታ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ በሀገር በቀል ቋንቋዎች ልማትና ቴክኖሎጂ ላይ እያከናወነ ያለውን አበረታች ሥራም አድናቀዋል። ከውይይቱ በተጨማሪ የልዑካን ቡድኑ የኢንስቲት
ዩቱን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የቴክኖሎጂ ልማቶችና የመሠረተ ልማት ዝግጅቶችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute