የአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምዕራፍ፡ አህጉሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ ዝግጁ ናት?
· AI Investment
Artificial intelligence could add more than $1 trillion to Africa’s economy by 2035, with Ethiopia emerging as a strategic AI hub by leveraging renewable energy, digital infrastructure, local data, and context-driven innovation.
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለ አፍሪካ ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡: በዘርፉ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ይህን እድገት ተጨባጭ ለማድረግ
ወሳኝ ነው። በዚህም እስከ 2035 ድረስ የአፍሪካ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ማደግ ይችላል። ይሁን እንጂ ይህ ኢኮኖሚያዊ እድገት ስትራቴጂያዊ ለውጥ ማድረግን ይጠይቃል። ከዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ግዙፍ ኩባንያዎች ጋር ከመወዳደር ይልቅ የዕለት ተዕለት እና አካባቢያዊ ችግሮችን በመፍታት ላይ ማተኮር ያስፈልጋል።
በአፍሪካ ልማት ባንክ ድጋፍ በባዛራ ቴክ (Bazara Tech) የተካሄደ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ኤአይ መሰረታዊ ዘርፎችን ሙሉ በሙሉ መቀየር ይችላል። ለምሳሌ በግብርና ዘርፍ የምርት መጠንን በማሳደግ እና የአየር ሁኔታን በመተንበይ በኩል ኤአይ ትልቅ ጥቅም አለው፡፡በንግድ እና ማምረቻ ዘርፍ ደግሞ የጅምላ፣ የችርቻሮ ንግድ እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ሎጂስቲክስን በማቀላጠፍ እና አውቶሜሽንን በመጠቀም ማሻሻል ይቻላል። በተጨማሪም የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት እንዲሁም የጤና ጥበቃ ስራውን በማሻሻል ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው።
ይህ ትልቅ አቅም ቢኖርም በአፍሪካ አስተማማኝ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ኤሌክትሪክ ዋናው ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፤ የዳታ ማዕከላት ከፍተኛ የሆነ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋሉ። እንዲሁም የኔትወርክ ሽፋን እየሰፋ ቢሄድም፣ በስማርት ስልኮች ውድ ዋጋ የተነሳ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካዊያን ዘመናዊ ዲጂታል መሣሪያዎችን እንዳይጠቀሙ አግዷቸዋል። ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ለአፍሪካዊያን ተሞክሮ የሚሆን አቅም አላት። ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጨምሮ ሰፊ የታደሽ ሃይል ሃብቶቿን በመጠቀም ዘርፉ የሚፈልገውን ሃይል እያቀረበች ነው፤ ይህም ለአህጉራዊ ዲጂታል ሽግግር እና ሉዓላዊነት ትልቅ አርዓያ ይሆነናል።
አፍሪካ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ሞዴሎችን ለመድገም ከመሞከር ይልቅ፣ በአካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ፈጠራን ማበረታታት እንዳለባት ጥናቱ ይጠቁማል። ዓለም አቀፍ ሞዴሎች ሊዘነጓቸው የሚችሉትን በግብርና እና በጤና ዘርፍ ያሉ የበለጸጉ ሀገር በቀል መረጃዎችን በመጠቀም አፍሪካዊ ፈጣሪዎች የተሻሉ እና ዒላማቸውን የጠበቁ መፍትሄዎችን ማበልጸግ ይችላሉ። ለስኬቱ ሁለት ነገሮች አብረው መሄድ አለባቸው፦ የታዳሽ ሃይል መሠረተ ልማትን በገንዘብ መደገፍ እና በአህጉሪቱ የሚገኙ ንቁ ዲጂታል ሥራ ፈጣሪዎችን ማበረታታት። ኢትዮጵያ ይህን አካሄድ በመተግበር አሁንም የበርካታ አፍሪካ ሀገራት የተሞክሮ ምንጭ ናት፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute