የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የኤ.አይ ክበብ አቋቋመ።
· Education
An AI club was established at Etege Menen Girls' Boarding High School with support from the Ethiopian Artificial Intelligence Institute, aiming to empower students with practical skills and innovation in artificial intelligence.
በክበብ ምስረታ መርኃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ ከበደ ቶሎሳ የኤ.አይ ክበቡ አባላት ለዉጤታማነት በተነሳሽነት ሁሌም የሚሰሩ እንዲሆኑ አሳስበዋል። የጽ/ቤት ኃላፊዉ አክለዉም ኢንስቲትዩቱ ተማሪዎቹን አስፈላጊ በሆነበት ጉዳይ ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አመላክተዋል።
በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ም/ርዕሰ መምህር ሀብታሙ ዱጉማ በበኩላቸዉ ት/ቤቱ አቅም ያላቸዉ ተማሪዎች እና መምህራን መገኛ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ተማሪዎቹ ያላቸዉን እዉቀት ተግባራዊ ወደሆነ ክህሎት የሚቀይሩበትን ድጋፍ ከኢንስቲትዩቱ እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
የክበቡ አባላት በቀጣይ ሊሰሩ ስለታቀዱ ስራዎች ገለጻ በማቅረብ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ ለመሆን ያላቸዉን ፍላጎት አስታዉቀዋል።
ከኤ.አይ ክበብ ምስረታው ጎን ለጎን በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ዉስጥ ጉብኝት ተካሂዷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute