አቡዳቢ የኤአይ አጠቃቀምን ለማስፋፋት ከኦፕንኤአይ ጋር መስራት ጀመረች
· AI Investment
Abu Dhabi and OpenAI Partner to Expand AI Across Government, Education, Investment, and Food Sectors
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አካል የሆነችው አቡዳቢ ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመንግሥት አስተዳደር፣ በትምህርት፣ በኢንቨስትመንትና በምግብ ዘርፎች
ውስጥ በስፋት ለመተግበር ከዓለም አቀፉ የኤአይ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ኦፕንኤአይ ጋር ስትራቴጂያዊ ትብብር ጀመረች።
ትብብሩ የተመሠረተው የአቡዳቢ ልዑልና የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼክ ካሊድ ቢን መሐመድ ከኦፕንኤአይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳም አልትማን ጋር
ባደረጉት ውይይት ላይ መሆኑን ዘ ናሽናል የተሰኘው የዜና ምንጭ ዘግቧል።
በትብብሩ መሠረት ኤአይን በተለያዩ የልማት ዘርፎች በማቀናጀት የመንግሥት አገልግሎቶችን የበለጠ ፈጣንና ቀልጣፋ ማድረግ፣ የትምህርት ሥርዓቱን ማዘመን፣ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን መፍጠርና በምግብ ዘርፍ ያለውን የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ ትኩረት ይደረግባቸዋል።
ይህ ትብብር አቡዳቢ ኤአይን ከቴክኖሎጂ ዘርፍ ባሻገር በመንግሥታዊና በማኅበራዊ አገልግሎቶች ውስጥ በማቀናጀት የዲጂታል ለውጧን ለማፋጠን እየወሰደች
ያለው ሰፊ እርምጃ አካል ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute