ዲጂታል የጤና ሥርዓቶች ጠንካራ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ በመፍጠር ረገድ ያላቸው ሚና ላይ የሚያተኩር የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
· Education
EAII highlighted the role of AI in improving healthcare and strengthening regional collaboration on digital health.
በዓለምባንክ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም በጤና ሚኒስቴርተባባሪ አዘጋጅነት የተሰናዳው የምክክር መድረክ በምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካየሚገኙ የጤና፣የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ተቋማትን ያሰባሰበ ነው። በወርክሾፑላይ ፓናሊስት የነበሩት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የኤ.አይቴክኖሎጂን በዘርፍ አቀናጅታ በመጠቀም ያላትን ተሞክሮ አካፍለዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የጤናዉን ዘርፍ ከኤ.አይ ቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ዉጤታማነትን ማሳደግ እንዲሁም ይበልጥ ተደራሽ ማድረግ እንደሚቻል በማንሳት፤ ይህንንም ዕውን ለማድረግ ኢንስቲትዩቱ ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በዘርፉ ውጤታማ ለሆነ የኤ.አይቴክኖሎጂ ልማት የጤናባለሙያዎች፣ የቴክኖሎጂው አልሚዎች እና የመንግሥት አካላትን በትብብር የመስራት አስፈላጊነት ምክትል ዋና ዳይሬክትሩ አብራርተዋል። የኤ.አይ ቴክኖሎጂንበሥነ-ምግባራዊ መርህ መምራት አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ አግባብ መስራት እንደሚገባም አጽንኦት
ሰጥተዋል።
ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ ላይ ተሳታፊዎች የዲጂታል የጤና መፍትሄዎችን በማስፋፋት ዙሪያ ያላቸውንልምድ ያካፍላሉ፡፡ መድረኩ ዘርፉ ላይ ባተኮሩ ፖሊሲ እናደንቦች ዙሪያ ከመወያየት ባሻገር፥ ተሳታፊዎች ዲጂታል ክህሎቶችን የሚያጠናክሩበት እንዲሁም ዘላቂ እና ጠንካራ የጤና አጠባበቅ ስርዓቶችን ለመገንባት ትብብር ለመፍጠር ያስችላል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute