የግብርና ዘርፉን በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለመደገፍ የተዘጋጀው የግብርና Collaborative AI Studio Challenge ስልጠና እና ውድድር ተጠናቀቀ፡፡
· Education
Agriculture AI Studio Challenge Concludes with Innovative Projects, Awards, and Startup Support
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) በጋራ ባዘጋጁት የግብርና Collaborative AI Studio Challenge ለአስር ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ስልጠና የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት ቴክኖሎጂ ዛሬ ተሠርቶ የሚቆም ሳይሆን በተከታታይ የሚሻሻልና የሚለወጥ በመሆኑ የፈጠራ ሃሳብቸውን በቁርጠኝነትና በትጋት ከዳር ማድረስ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ሰልጣኞች በስልጠናው በሐሳብ ደረጃ የያዙትን የኤ.አይ መፍትሔ ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል ክህሎት አግኝተዋል። በማጠቃለያው መርሐ ግብሩ የኤ.አይ
መፍትሔ ፕሮጀክቶቻቸውን አቅርበው በተወዳደሩበት መድረክ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ የወጡ ቡድኖች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በውድድሩም አንደኛ የወጣው ቡድን 550,000 ብር፣ ሁለተኛ የወጣው ቡድን 400,000 ብር፣ ሦስተኛ የወጣው ቡድን 250,000 ብር ተሸልመዋል።
ሰልጣኞች ቴክኖሎጂውን በደንብ ለመረዳትና ሐሳባቸውን አጠንክረው ወደ ተጨባጭ ምርት ለመቀየር የሚያስችል ተግባራዊ እውቀት እንዳገኙ ገልጸዋል። ፕሮጀክታቸውንም ወደ ተግባራዊ ምርት ለመቀየር በኢንስቲትዩቱ የስታርታፕ ማዕከል ድጋፍ ያገኛሉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute