ጉግል ለአፍሪካ የይዘት ፈጣሪዎች የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ተደራሽነትን ማስፋፊያ የ1 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡
· Other
Google and Idris Elba Launch $1 Million AI Initiative to Empower African Creators and Accelerate the Digital Creative Economy
ጉግልከእንግሊዛዊዉ ተዋናይ እና ስራ ፈጣሪኢድሪስ ኤልባ ጋር በመተባበርየአፍሪካውያን የፈጠራ ባለሙያዎች የኤ.አይ ቱሎችንተደራሽነትን ለመጨመር ያለመ የ1 ሚሊዮንዶላር ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡ በተለይም ዋጋቸዉ ከፍተኛ የሆኑ የፕሮዳክሽን ግብዓቶችን ማግኘት ለሚቸገሩ ባለሙያዎች በአነስተኛ ወጪ ከፍተኛ ጥራት ያለው ይዘትእንዲሰሩ ለመርዳት የሚያስችል ነዉ።
ፕሮጀክቱ በጉግልእና በኤልባ ሆፕ ፋውንዴሽን በጋራ የገንዘብድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ብሉምበርግ በዘገባዉ አስታዉቋል።
ይህ ፕሮጀክት በጆሃንስበርግ በተካሄደው የጎግል ኤ.አይ ስብሰባላይ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ጋና፣ ኬንያ እና ሴራሊዮንለሚገኙ 100,000 የሚጠጉ የፈጠራ ባለሙያዎች የጎግልን ዲጂታል ምርቶችን በነጻ ተደራሽ ያደርጋል።
ሞርዶር ኢንተለጀንስ (Mordor Intelligence) የተባለው የገበያ ጥናት ተቋም መረጃ እንደሚያሳየው የአፍሪካ ሚዲያ እና መዝናኛ ኢንዱስትሪ ገበያ 93 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለዘርፉ ዕድገት ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ይጠበቃል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute