የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መሥሪያ ቤትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
The officials from the Information Network Security Administration (INSA) visited the new headquarters of the Ethiopian Artificial Intelligence Institute.
በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለኢመደአ አመራሮች የተቋሙን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ኢንስቲትዩቱ ተልዕኮውን በላቀ ደረጃ ለመወጣት የሚያስችል አደረጃጀት እና ለሰራተኞች ምቹ የሆነ የሥራ ከባቢ መገንባቱን በጉብኝታቸው መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም ሀገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን ለማፋጠን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ጉብኝቱ ደህንነቷ የተጠበቀ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁለቱ ተቋማት ያላቸውን ትብብር እና ቅንጅት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያስቻለ ነው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute