የኤአይ ስታርታፕ ኢንኩቤሽን ሰልጣኞች ተመረቁ::
· Education
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute has graduated its first cohort of startups following six months of intensive training, mentorship and support designed to transform innovative ideas into market-ready solutions.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የኤአይ ስታርታፕ ማዕከል ባለፉት ስድስት ወራት በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ስታርታፖች
አስመረቀ።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ ዕለቱ የመደመር መንግሥት ራዕይና የኢትዮጵያ የመፈጸም አቅም በተግባር የታየበት መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ተመስገን ለምርቃቱ ክብር የበቁትን ስታርታፖች እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት፣ በፈጠራ ሥራዎቻቸው ሁሉ ለኢትዮጵያ ብልጽግና ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ስታርታፖቹ ከሐሳብ ደረጃ ተነስተው ወደ ምርት እስከ ተሸጋገሩበት ጊዜ ድረስ ልዩ ክትትልና ድጋፍ ሲደረግላቸው መቆየቱን ገልጸዋል። አያይዘውም ከኢንስቲትዩቱ ምስረታ ጀምሮ የስታርታፕ ማዕከሉ ለዚህ ስኬት እንዲበቃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላደረጉት ጠንካራ አመራርና ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ሰልጣኞቹ በማበልጸጊያ ቆይታቸው ምቹ የሥራ ቦታና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኙ ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ መሪዎች፣ ከፖሊሲ አውጪዎች፣ ከኢንቨስተሮችና ከሳይንስ ማኅበረሰቡ ጋር የመገናኘትና ሰፊ የትስስር ዕድል አግኝተዋል። ይህም መልካም ተፅዕኖ እንዲፈጥሩ፣ እውቅናቸውን እንዲያሳድጉና ዕድሎቻቸውን እንዲያሰፉ አስችሏቸዋል።
በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያም በኤአይ የተፅዕኖ ፈጣሪነት ሽልማት፣በኤአይ የላቀ ብቃት ሽልማት፣ በሴቶች ለተመሩ ስታርታፖች የሚሰጥ የላቀ ሽልማት ፣ የተስፋ ሰጪ ስታርታፕ ሽልማት እና የፈጠራ ሥራ ሽልማት ዘርፎች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ስታርታፖች ከእለቱ የክብር እንግዳ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute