“ከቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽን ጀርባ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አለ፡፡” የአሐዱ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ
· Visiting
Executives from Ahadu Bank visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to explore AI-driven solutions for modernizing banking services and strengthening future collaboration.
ለስራ ኃላፊዎቹ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል። ም/ዋና ዳይሬክተሩ በገለፃቸው ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ መስኮች ችግሮችን መቅረፍ የሚችሉ እና የተቋማትን አገልግሎት የሚያዘምኑ የሰውሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማልማት ጥቅም ላይ እያዋለ መሆኑን ተናግረዋል።
የአሐዱ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ትራንስፎርሜሽን ጀርባ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መኖሩን በጉብኝታቸው ማስተዋላቸውን ተናግረዋል። የኢንስቲትዩቱ ህያውነት አንድ እርምጃ ቀድሞ የማሰብ ውጤት ነው ያሉት አቶ አንተነህ፤ ባንኮች ቴክኖሎጂውን ተጠቅመው አገልግሎታቸውን ለማዘመን እና ለማሻሻል ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።
ጉብኝቱ ቴክኖሎጂውን ለማልማት እና በቀጣይነት ተባብረው መስራት የሚያስችላቸውን ጉዳዮች መለየት ያስቻለ ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute