ከጌጣጌጥ ወደ ቺፕ
· AI Investment
Chinese Lab-Grown Diamond Producers Target AI Chip Cooling and Quantum Technology Markets
በቤተ ሙከራ አልማዞችን የሚያመርቱ የቻይና ኩባንያዎች የጌጣጌጥ ገበያው አዋጭነት እየቀዘቀዘ በመምጣቱ አዲስ መላ እየፈለጉ ነው። መልሱን ያገኙት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በሴሚኮንዳክተር ዘርፍ ውስጥ ነው።
አልማዝ ሙቀትን ከሌላ ማንኛውም ቁሳቁስ በተሻለ የመቋቋም ችሎታ አለው። ይህን በመጠቀም ኩባንያዎቹ ከቺፖች የሚወጣውን ሙቀት ለማቀዝቀዝ እና ለኳንተም ቴክኖሎጂዎች የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ከአልማዝ እያዘጋጁ ነው።
ኤአይ እየተስፋፋ ሲሄድ ቺፖችን በብቃት ማቀዝቀዝ ቁልፍ በመሆኑ አልማዝ በባህሪው ቺፖች ውስጥ ዛሬ የሚሠራባቸውን ቁሳቁሶች ሊተካ ይችላል።
ይህ እንቅስቃሴ ቤጂንግ የወጪ ንግድ ገደቦች እየበረቱ ባሉበት ወቅት በቴክኖሎጂ ራስን ለመቻል ከምታደርገው ጥረት ጋር ይስማማል።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ መንገዱ ቀላል አይደለም። ምርቱ ውድ ነው፤ ወደ ነባሩ የቺፕ አመራረት ሂደት ለማስገባትም ተጨማሪ ምርምርና ልማት ያስፈልጋል። ተንታኞች ቴክኖሎጂው ከፍተኛ ዋጋ ሊያስገኝ የሚችል ስትራቴጂካዊ ጥቅም እንዳለው ቢስማሙም ምን ያህል በስፋት ማምረት እንደሚቻልና ወደ ገበያ የሚገባበት ትክክለኛ ጊዜ ላይ እርግጠኛ አይደሉም።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute