የኤ.አይ ሴንሰሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ አቅመ ዳካማና አዛውንቶች በቤት ውስጥ ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩ እየረዱ ነው፡፡
· AI Solutions
AI-Powered Care System “Lilli” Enables Independent Living and Saves £1.6 Million for Medway Council.
በእንግሊዝ ሜድዌይ ጥቅም ላይ ለዋለዉ አዲስ የእንክብካቤ ቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ አዛውንት እና አቅመዳካሞች በቤት ውስጥ የበለጠ ደህንነታቸው ተጠብቆ እና እራሳቸውን ችለው እየኖሩ ነው።
ሊሊ ተብሎ የሚጠራው ቴክኖሎጂ የአንድን ሰው የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ለመረዳት አነስተኛ ሴንሰሮች እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ይጠቀማል።
ቴክኖሎጂው ያለ ካሜራ ወይም ማይክሮፎን የሚሰራ ሲሆን በምትኩ ትናንሽ ሴንሰሮችን በመጠቀም እንቅስቃሴን ፣ መብላትን፣ መተኛትን፣ የመታጠቢያ ቤት አጠቃቀምን እና የቤት ሙቀትን ይከታተላል።
ስርዓቱ የበሽታ ምልክቶች፣ የእንቅስቃሴ መቀነስ፣ ወይም በሌሊት የሚደረግን አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ሲመለከት ምልክት ይሰጣል፡፡ ይህም ተንከባካቢዎች ቀደም ብለው ምላሽ እንዲሰጡ እና ለግለሰብ ፍላጎቶች ድጋፍን እንዲያመቻቹ ይረዳል።
ቴክኖሎጂው በመጀመሪያው አመት ብቻ የ1.6 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ለመቆጠብ ማስቻሉን የዘገበው ቢ.ቢ.ሲ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute