ሩሲያ በኤአይ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማጠናከር ከብሪክስ ሀገራት ጋር አዲስ ጥምረት አስጀመረች
· Other
Russia Launches International AI Alliance to Strengthen BRICS Cooperation and Technology Transfer
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ከብሪክስ አባል ሀገራት እና ሌሎች አጋሮች ጋር በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን ትብብር
የሚያጠናክር አዲስ ዓለም አቀፍ ጥምረት መመስረቷን አስታውቀዋል።
በሩሲያው ስበርባንክ(Sberbank) አስተባባሪነት የተዘጋጀው ይህ ጥምረት በዘርፉ የጋራ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማጎልበትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን
ለማሳደግ ያለመ ነው። ኢትዮጵያም የብሪክስ አባል ሀገር እንደመሆኗ ከዚህ ስትራቴጂካዊ ትብብር የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ሽግግር ለማግኘት ትልቅ እድል ይፈጥርላታል።
በቅርቡ በሩሲያ በተካሄደው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ ላይ ቻይና በኤአይ ቴክኖሎጂ ዙሪያ የክፍት ምንጭ(open source) ትብብር እና የጋራ ምርምር
ለማድረግ ያቀረበችውን ጥሪ መነሻ በማድረግ ይህ አዲስ ጥምረት የደቡብ ዓለም (Global South) ሀገራትን የኤአይ እድገት የሚያፋጥን መልካም ዕድል እንደሚሆን ይጠበቃል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute