የኤም.አይ.ቲ ተመራማሪዎች ታሪካዊ መረጃዎች ሳያስፈልጉት የከፋ የአየር ሁኔታን የሚተነብይ ኤ.አይ ሞዴል ይፋ አደረጉ፡፡
· AI Solutions
MIT researchers have developed “η-learning,” a machine-learning method capable of generating plausible extreme weather scenarios beyond historical records, helping cities assess risks to infrastructure, power systems and emergency preparedness.
የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (MIT) ተመራማሪዎች ታሪካዊ መረጃዎችን እንደ ዋቢ ሳይጠቀሙ ከዚህ ቀደም ታይተው የማይታወቁ የአየር ሁኔታዎችን አስቀድሞ መተንበይ የሚያስችል አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አስተዋውቀዋል።
"η-learning" ተብሎ የተሰየመው ይህ ቴክኖሎጂ ከነባር የአየር ሁኔታ ሞዴሎች በተለየ መልኩ ቀደም ሲል ከተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች መረጃ ላይ ጥገኛ ሳይሆን በስታቲስቲክስ ስሌት ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን መተንበይ ያስችላል።
የምርምሩ ባለቤቶች እንደገለጹትሞዴሉ የክስተቶችን ድግግሞሽ የሚያሳዩ የስታቲስቲክስ መረጃዎችን እና የቦታ ስርጭት ካርታዎችን በማጣመር ይሰራል። ለምሳሌ በኒውዮርክ ከተማ በታሪክ ከተመዘገበው 200 ሚሊሜትር የዝናብ መጠን በላይ የሆነን የ 300 ሚሊሜትር ማዕበል ስጋት በትክክል ማሳየት ችሏል።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኒውስ እንደዘገበው ይህ አዲስ ግኝት ከተሞች በ100 ዓመት አንዴ ሊከሰቱ የሚችሉ የከፋ አደጋዎችን አስቀድመው በመገመት የመሰረተ ልማት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል እና የአደጋ ጊዜ ዝግጅታቸውን እንዲፈትሹ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute