የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኙ
· Visiting
Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption Commission Explores AI Solutions to Improve Efficiency, Transparency, and Anti-Corruption Efforts
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመገኘት የስራ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱ ወቅትም የኢንስቲትዩቱን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የለሙ ሀገር በቀል የኤ.አይ ስርዓቶችን በስፋት ተመልክተዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ እውን ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል። በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ የፌዴራል የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንን ጨምሮ ለተለያዩ ተቋማት ስራዎችን የሚያቀላጥፉ እና አሰራርን የሚያዘምኑ የኤ.አይ ስርዓቶችን ማልማቱን አስታውሰዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ቢሮ ሰራተኞች በበኩላቸው በጉብኝቱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሙስናን ለመከላከልና ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሊያበረክት የሚችለውን ሰፊ አስተዋጽኦ በጥልቀት መገንዘባቸውን ገልጸዋል።
በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ ላይ የቢሮውን አገልግሎቶች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በማዘመን ቀልጣፋና ግልጽ አሰራር ለመዘርጋት የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute