የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ግዙፍ ኩባንያ አንትሮፒክ (Anthropic) የክሎድ (Claude) ኤ.አይ አገልግሎትን በኢትዮጵያ ጀመረ፡፡
· Other
Anthropic Launches Claude AI in Ethiopia to Expand Digital Innovation, Research, and Productivity
የኢትዮጵያን የዲጂታል ምህዳር ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እድል ነው። በአሜሪካው ታዋቂ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር ተቋም አንትሮፒክ (Anthropic) የሚበለጽገውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተመራጭነት ያለው ክሎድ (Claude AI) አገልግሎት በኢትዮጵያ በይፋ ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።
ይህ ስኬት እውን እንዲሆን ካስቻሉ ተቀዳሚ ምክንያቶች መካከል የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከአንትሮፒክ የፖሊሲ እና የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አኒ ማክስዌል ጋር ያደረገዉ ተከታታይ፣ ውጤታማና ስልታዊ የዲፕሎማሲ ውይይቶች ተጠቃሽ ናቸው።
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኖሎጂ አፍቃሪዎች፣ ሶፍትዌር አበልጻጊዎች እና ተመራማሪዎች እነዚህን የላቁ የኤ.አይ መሣሪያዎች ለመጠቀም ይቸገሩ ነበር። አሁን ግን በተደረገው ከፍተኛ ቴክኒካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ኢትዮጵያ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ መካተት ችላለች። ይህም ተጠቃሚዎች የክሎድን የላቁ የኮዲንግ፣ የዳታ ትንተና እና የጥልቅ ምርምር አገልግሎቶች እንዲጠቀሙ በር ከፍቷል።
ይህ ጅምር ሀገሪቱ የነደፈችውን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዕውን ለማድረግ እና ለሀገር በቀል የፈጠራ ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን የኤ.አይ መሰረተ ልማቶች ለማቅረብ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው።
የክሎድ አገልግሎትን አሁን ላይ በድረ-ገጽ ማለትም claude.ai ኦፊሴላዊ ሊንክ በመጠቀም፣ እንዲሁም በiOS እና በAndroid መተግበሪያዎች አማካኝነት ማግኘትና መጠቀም ይቻላል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute