“ኤ.አይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያመጣው ለውጥ ከምንጠብቀው በእጅጉ የላቀ ነው፡፡” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
· AI Solutions
Prime Minister Abiy Ahmed Praises EAII’s Transformative Role in Advancing Ethiopia’s AI Innovation and Strengthening National Technological Capacity.
በዛሬው ዕለት በተካሄደው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተገኝተዉ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ ውስጥ ያመጣው ለውጥ ከሚጠበቀው በእጅጉ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በማሳየነትም በውጭ ሀገር ከፍተኛ ገንዘብ የተጠየቀበትን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የሶፍትዌር ልማትን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩቱ በነጻ ሰርቶ መስጥቱን ጠቁመዋል፡፡ የሀገሪቱን ወጪ እና ገቢ የንግድ እንቅስቃሴ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ውጤታማ እንዲሆን ለጉምሩክ ኮሚሽን የለሙት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ውስጥ የኢንስቲትዩቱ ድርሻ ጉልህ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ለቀጣዩ ትውልድ ሲታሰብ የሚያኮራ ተቋም መገንባቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አንስተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute