የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልዑክ ኢንስቲትዩቱን ጎበኘ።
· MOU
Led by Supreme Court President Ali Badru, the delegation explored EAII’s research projects and technological capabilities, with discussions focused on leveraging digital solutions to modernize judicial operations in the Somali Region.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ልዑካኑን ተቀብለዉ የኢንስቲትዩቱን አጠቃላይ ስራዎች አስጎብኝተዋል።
የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አሊ ባድሩ በኢንስቲትዩቱ ባዩት ነገር ኩራት እንደተሰማቸዉ ገልጸዋል። አክለዉም የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የዘመነ ለማድረግ የሚያስችል ዉይይት መደረጉንም አስታዉቀዋል።
ልዑካኑ በኢንስቲትዩቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኙ የምርት ማሳያ፣ የሮቦቲክስ ወርክሾፖችን እንዲሁም የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋዉረዉ ተመልክተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute