የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
Enhancing Coordination for Digital Transformation
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ የተመራው ልዑክ አዲሱን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት ጎብኝቷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ስለ ኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ እና ስለአዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት ገለፃ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስክ የፈጠረችው አቅም በከተማ ደረጃ የተጀመሩ የልማት እና አገልግሎትን የማዘመን ተግባራትን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም የሚያስችል መሆኑን ከፍተኛ አመራሮቹ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute