ኢትዮጵያና ቻይና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ ውይይት ተካሄደ፡፡
· Visiting
Ethiopia and China Deepen AI Cooperation to Advance Technology Transfer, Economic Growth, and National Productivity.
የኢትዮጵያ እና የቻይናን ዘመን ተሻጋሪና ሁለንተናዊ ወዳጅነት ይበልጥ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ የሁለትዮሽ ውይይት በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተካሂዷል።
በአፍሪካ ህብረት የቻይና ልዑክ መሪ አምባሳደር ጃንግ ፋንግ የተመራው የልዑካን ቡድን በኢንስቲትዩቱ የሥራ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በጋራ ልማት ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር ተካሂዷል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ ባደረጉት ገለጻ፣ ተቋሙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ የፈጠራ ሥራዎችን በማበልጸግ በሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ እያበረከተ ያለውን ስትራቴጂካዊ ተግባራት አብራርተዋል። ኢንስቲትዩቱ በጤና፣ በግብርና እና በዲጂታል መሠረተ ልማት ዘርፎች እያመጣ ያለውን ተጨባጭ ለውጥም ለልዑካኑ አስረድተዋል።
ጉብኝቱን ተከትሎ በተካሄደው ውይይት፣ የቻይና-አፍሪካን ትብብር ማዕቀፍ በማድረግ የኢትዮጵያ እና ቻይና የቴክኖሎጂ ትብብርን ከፍ ማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ተሰጥቷል። አምባሳደር ጃንግ ፋንግ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያሳየች ያለውን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ አድንቀው፣ ቻይና በዚህ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መስክ ያላትን ልምድና ዕውቀት ለማጋራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute