የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከዋድዋኒ ኤ.አይ ግሎባል (Wadhwani AI Global) ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
· MOU
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute has signed an MoU with Wadhwani AI Global to strengthen collaboration in AI research, innovation, and real-world applications.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በዓለማቀፍ ደረጃ በኤ.አይ ምርምርና ልማት ላይ ከሚሰራው የህንዱ "ዋድዋኒ ግሎባል ኤ.አይ" ተቋም ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በኢትዮጵያና በህንድ መካከል ያለው ታሪካዊ ግንኙነት ለረጅም ዓመታት የዘለቀ መሆኑን ጠቅሰዋል። በተለይም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ መሪነት ግንኙነቱ ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት መጠናከሩን ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።
የዋድዋኒ ግሎባል ኤ.አይ ሥራ አስኪያጅ ዳክሻ ባራድዋጅ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር ስምምነት በመፈረማቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። ሥራ አስኪያጁ አያይዘዉም በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ተጠቃሚነት ዙሪያ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ዉጤታማ ስራ ለማስመዝገብ ስምምነቱ ቁልፍ የትብብር ማዕቀፍ መሆኑን ጠቁመዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute