ታዋቂው ቲክቶከር ዲላን ፔጅ (Dylan Page) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ።
· Visiting
Global Influencer Dylan Page Praises Ethiopia’s AI Innovation and Africa’s Rising Digital Transformation
ዲላን ፔጅ በመባል የሚታወቀው የዲጂታል ጋዜጠኛ እና የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ በኢንስቲትዩቱ በመገኘት የተቋሙን ስራዎች ተመልክቷል፡፡
ዲላን ፔጅ ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጠዉ አስተያየት “ይህ ጉብኝት በዓለማቀፍ ደረጃ ስለ አፍሪካ ያለውን የተዛባ አመለካከት የሚቀይር ነው። ይህን በቴክኖሎጂ የተቃኘ ቦታ ሳየዉ ተደምሜያለሁ። በጣም ያማረና አስደናቂ ቦታ ነዉ። አፍሪካ ተቀይራለች አዲሱን ገፅታዋን ለዓለም የሚያሳይ ቦታ ሆኖ አጊኝቼዋለሁ። ባየሁት ነገር ደስተኛ ነኝ።” ሲል ገልጿል።
ዲላን በተለይም ለወጣቶች በሚመች መልኩ በፈጣን አቀራረብ፣ አጭር፣ ሳቢ እና ለመረዳት ቀላል የሆኑ ዓለማቀፍ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በማቅረብ ይታወቃል።
በቲክቶክ ከ19 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው ዲላን፥በራሱ ልዩ የአቀራረብ ዘይቤ ዓለማቀፍ ተከታዮችን ማፍራት የቻለ ሲሆን፤ በተለይም ወጣቱን ትውልድ ዜና የሚቀበልበትን መንገድ በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute