በዛሬው ዕለት የተካሄደውን የUnified MESOB Platform ምርቃት አስመልክቶ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ያስተላለፉት መልዕክት
· Other
Prime Minister Abiy Ahmed Launches Africa’s First Unified MESOB Platform, Advancing Digital Government, Transparency, and National Productivity
"በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የበለጸገው እና በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነው Unified MESOB Platform በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ዛሬ ተመርቆ በይፋ ወደ አገልግሎት ገብቷል፡፡
ይህ ፕላትፎርም ለሀገራችን የዲጂታል ሽግግር ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ ነው። '‘ዲጂታል ለልህቀት'’ ጉባኤ አካል የሆነው እና ዛሬ አገልግሎት የጀመረው ይህ የተቀናጀ የዲጂታል ፕላትፎርም በክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን ግልፅ አቅጣጫ አመልካችነት የቴክኖሎጂ አቅማችንን በራሳችን እጆች መገንባት እንደምንችል ያሳየ ታላቅ ስኬት ነው። በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ ያደረጉት ከፍተኛ እምነትና ድጋፍ ተቋማችን የዜጎችን ጊዜ የሚቆጥብ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታ እና የመንግስት ተቋማትን አሰራር ግልፅነትና ታማኝነት የሚያጎለብት ዘመናዊ የዲጂታል መሰረተ ልማት እንዲፈጥር አስችሎታል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዚህ ራዕይ መሳካት ላደረጉት የማያቋርጥ ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን።
መተግበሪያው በአፕ ስቶር እና በፕሌይ ስቶር ለስማርት ሞባይል ተጠቃሚዎች እንዲሁም ለኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ደግሞ በድረ ገፅ አማካኝነት ቀርቧል።
ይህንን ስኬት በጋራ በማጠናከር ልምዳችንን ለአፍሪካ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ለማካፈል እና ወደፊትም በቴክኖሎጂ የተደገፉ የላቁ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ሙሉ ዝግጁ መሆናችንን ለመግለጽ እወዳለሁ።"
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute