ሶፍትባንክ ግሩፕ በኦፕን ኤ.አይ የ11 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለንዋይ ሊያፈስ ነዉ።
· AI Investment
SoftBank Plans Nearly $11 Billion Bond Sale to Finance Its OpenAI Investment and Expand Global AI Infrastructure
የጃፓኑ ሶፍትባንክ ኩባንያ በኦፕን ኤ.አይ ያለውን ኢንቨስትመንት ለመደገፍ11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ቦንድ ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኩባንያው 10 ቢሊዮን የሚያወጣ ቦንድ በዶላር እንዲሁም 1 ቢሊዮን የሚያወጣ ቦንድ በዩሮ ለመሸጥ እየተዘጋጀ ነው።
ከቦንድ ሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ ሶፍትባንክ ግሩፕ በኦፕን ኤ.አይ ፈሰስ ለሚያደርገዉ መዋዕለንዋይ የሚዉል መሆኑ ተነግሯል። የቦንድ ሽያጩ በታቀደው መጠን ከተጠናቀቀ 7 ኢለቨን (7-Eleven) የተሰኘዉ ኩባንያ በአዉሮፓዊያኑ 2021 ይዞት የቆየውን የ10.93 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ሽያጭ ሪከርድ የሚሰብር ይሆናል። የተዘጋጀዉ ቦንድ በተያዘዉ መስከረም የመጨረሻ ቀናት ለሽያጭ ለማቅረብ መታቀዱም ተገልጿል።
ሶፍትባንክ እና ኦፕን ኤ.አይ ከዚህ በፊት በጃፓን በኤ.አይ የታገዙ አገልግሎቶችን ለማጠናከር ብሎም በአሜሪካዉ የኤ.አይ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት (ስታርጌት ) ላይ በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute