የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማህበር ድጋፍ አደረገ።
· Other
The Ethiopian Artificial Intelligence Institute (EAII) has provided financial and material assistance to Mekedonia Home for the Elderly and Mentally Disabled, reaffirming its commitment to social responsibility alongside its research mission.
ኢንስቲትዩቱ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማህበር 1 ሚልዮን ብር እና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በድጋፍ መርሓ ግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ጥናትና ምርምሮችን ከማድረግ ጎን ለጎን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ መሆኑን ገልፀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ዶ/ር ቢንያም በለጠ የጀመራቸው የሰብዓዊነት ስራዎች ዛሬ ፍሬ አፍርተው እና በብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ገብተው በመንገድ ላይ የወደቁ በርካታ ወገኖቻችን በማንሳት የሚደረግላቸውን ድጋፍ በማየታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱም ከማሕበሩ ጎን ሆኖ በማገዝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ ክቡር ዶ/ር ቢንያም በለጠ በበኩላቸው መቄዶንያ በአሁኑ ወቅት ከ8500 በላይ አረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማንን በመርዳት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ላደረገላቸው ድጋፍ በመቄዶንያ አረጋውያን ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ከድጋፍ መርሓ ግብሩ በተጨማሪ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበርን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute