ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ግብይትን ለማቀላጠፍ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ሊጠቀም ነው፡፡
· AI Investment
Meta introduces generative AI-powered shopping features on Facebook and Instagram, enabling instant product insights, summarized reviews, and seamless in-app checkout.
ሜታ የፌስቡክ እና ኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ግብይታቸውን በገጾቹ ላይ በቀላሉ እንዲያከናውኑ እና የሸማቾችን ቁጥር ለመጨመር የሚረዱ አዳዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያዎችን ይፋ አደረገ።
ኩባንያው እንዳስታወቀው አዲሱ የቴክኖሎጂ አሰራር ደንበኞች ስለሚገዟቸው ምርቶች ዝርዝር መረጃ እንዲያገኙ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰዎች አስተያየቶችንማንበብ ሳያስፈልጋቸው፤ ኤ.አይ ሁሉንም አስተያየቶች አጠቃልሎ በአጭሩ እንዲያቀርብላቸው ይረዳል። በተጨማሪም ተጠቃሚዎች ከማህበራዊ ተጠቃሚዎች
ከማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ሳይወጡ በገጹ ላይ በሚገኝ የ"Buy Now" አማራጭ አማካኝነት ክፍያቸውን በአንድ ጊዜ መፈጸም ይችላሉ።
አገልግሎቱ ስለ ምርቱ ባለቤት (ብራንድ) ዝርዝር መረጃን፣ የሚመከሩ ተመሳሳይ ምርቶችን፣ ሊኖሩ የሚችሉ ቅናሾችን እና ሌሎች አጠቃላይ መረጃዎችንም አካቶ
የያዘ ነው።
ሜታ ይህን ያደረገው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦንላይን ገበያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ከመጣው ከቲክ ቶክ ጋር ያለውን ፉክክር ለመቋቋም እና ተጠቃሚዎች
ሳይንገላቱ በገጹ ላይ ምርቶችን እንዲገዙ ለማገዝ ነው።
እንደ ቴክ ክራንች ዘገባ ይህ እርምጃ ሜታ የደንበኞቹን የግብይት ልምድ ቀላል በማድረግ ሽያጭን ለማሳደግ የያዘው ስትራቴጂ አካል ሲሆን፤ በተለይም በኢንስታግራም በኩል የሚደረጉ ግብይቶችን ይበልጥ ሳቢ እና ፈጣን እንደሚያደርጋቸው ይጠበቃል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute