ፊፋ የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለመምራት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
· AI Solutions
FIFA plans to deploy advanced artificial intelligence systems during the 2026 FIFA World Cup to manage tournament operations, enhance refereeing transparency, and support all 48 participating teams.
የዓለማቀፉእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ የስራ ክንውኖቹን በኤ.አይ ላይ የተመሰረተ ለማድረግ ማቀዱን ይፋ አደረገ።ፊፋ ከሌኖቮ ኩባንያ ጋር በመተባበር ያቀረበው ይህ አዲስ አሰራር በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና አሜሪካ የሚካሄደውን ግዙፍ ውድድር ለመምራት ታላቅ ሚና ይኖረዋል።
በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር የቡድኖች ቁጥር ወደ 48 ማደጉና ጨዋታዎቹ በሦስት አገራት መካሄዳቸው ስራውን እጅግ ውስብስብ ያደረገው ሲሆን ለዚህ ደግሞ ኤ.አይን ትልቁ የመፍትሄ መሳሪያ አድርጎ ሊጠቀምበት አቅዷል፡፡
ፊፋ በዚህ ውድድር ሊተገብራቸው ያቀዳቸው የኤ.አይ ቴክኖሎጂዎች የውድድሩን ፍትሃዊነት እና ግልጽነት ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው፡፡ ይህም ለሁሉም 48 ቡድኖች እኩል የትንታኔ ዕድል የሚሰጠውን Football AI Pro፣ የዳኝነት ውሳኔዎችን ለተመልካች ይበልጥ ግልጽ የሚያደርገውን የተሻሻለ የዳኞች ካሜራ (Referee View)፣ እንዲሁም የ"ከጨዋታ ውጭ" ውሳኔዎችን በከፍተኛ ትክክለኛነት ለመለየት የሚያስችሉ የ3D ተጫዋቾች ምስሎችን (Avatars) ያካተተ ነው።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኒውስ እንደዘገበው እነዚህ ዘመናዊ አሰራሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ጨዋታዎችን እና ስታዲየሞችን በአንድ ማዕከል ሆኖ በብቃት ለመምራት የሚያስችል የመረጃ መቆጣጠሪያ ማዕከል ላይ የተገነቡ በመሆናቸው ውድድሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስኬታማ አመራር እንዲኖረው ያደርጋሉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute