አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በሕግ ሥራ ውስጥ ያለው ሚና
· Other
AI Advances Legal Services as Garfield AI Marks a Milestone in Faster, Fairer, and More Efficient Justice Delivery
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ፍትሃዊና ፈጣን የፍትህ አገልግሎት እንዲኖር እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው። የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውስብስብ የሆኑ መረጃዎችን በመመርመርና እውነታውን በጠበቀ መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ማስቻሉ ልዩ ባህሪው ነው። ይህም ድካምን፣ ጊዜንና ወጪን ለመቆጠብ አስችሏል።
ፋይናንሻል ታይምስ እንደ ዘገበው ፤በእንግሊዝ የሚገኘው ጋርፊልድ የተሰኘ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሕግ ቢሮ በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ውስጥ ጉዳይ በመርታት ታሪካዊ ምዕራፍ አስመዝግቧል። አገልግሎቱ በፍርድ ሂደት ውስጥ ድል ያስመዘገበው የመጀመሪያ የኤአይ የሕግ አገልግሎት ሆኖ ተመዝግቧል።
የጋርፊልድ ኤአይ መስራቾች እንደሚሉት ይህ ስኬት የሕግ አገልግሎቶችን ለማፋጠን፣ ድካምን ለመቀነስ እና እንግልት ለማስቀረት ያለው ፋይዳ የጎላ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute