የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ
· Visiting
Mozambique President Visits EAII, Praises Ethiopia’s AI Leadership and Calls for Africa’s Shared Growth Through Innovation
የሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ረገድ እያከናወነች ያለችውን መጠነ ሰፊ
ስራዎች ለፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል።
ፕሬዝዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ ብሩህ ተስፋ መሆኑን ገልጸዋል። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መጻኢውን የዓለም ሁኔታ የሚወስን በመሆኑ፣ ሁሉም ሀገራት በትኩረት ሊሰሩበት ይገባል ሲሉም አክለዋል።
ፕሬዝዳንቱ በኢንስቲትዩቱ ውስጥ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኘውን ወጣት የሰው ኃይል አድንቀዋል። ይህ የሰለጠነ ወጣት ኃይል ከኢትዮጵያ ባለፈ የአህጉሪቱን የወደፊት የዕድገት አቅጣጫ የሚወስን መሆኑን ጠቁመው፣ ወጣቱ በፈጠራ ስራ ላይ ተሰማርቶ ማየት ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ በተጨማሪም አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር ለአፍሪካ ፈጣን ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ በጋራ መስራትና ልምድ መለዋወጥ ለጋራ ብልጽግና መሰረት
መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute