የቀርጫንሼ ግሩፕ አመራሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
Institute and Kerchanshe Group explore AI integration in agriculture to boost innovation and productivity.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) እንግዶቹን ተቀብለዉ ስለ ኢንስቲትዩቱ የስራ እንቅስቃሴ ገለጻ አድርገዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በኢንስቲትዩቱ የሚከናወኑ የምርምር ስራዎችን በመግለጽ፥ በተለይም በግብርናዉ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ዉይይት ተደርጓል።
የቀርጫንሼ ግሩፕ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ እስራኤል ደገፋ (ዶ/ር) ሀገራችን በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመስራት ላይ የምትገኘዉን ስራ መመልከታቸዉን ገልጸዋል። የቡና ልማት ላይ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በትብብር ቢሰራ ዘርፉን በኤ.አይ ቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ዉጤታማ ብሎም ወጪ ቆጣቢ ማድረግ እንደሚቻል ከጉብኝቱ መገንዘባቸዉን ተናግረዋል።
የጉብኝት መርሓ ግብሩ የምርት ማሳያ፣ ዳታ ሴንተር፣ የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ ዲጂታል ቤተ መጽሐፍት እንዲሁም የስታርታፕ ማዕከልን ያካተተ ነበር፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute