“ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ታግዛ የምታካሄደው የድንበር ላይ ቁጥጥር አስደናቂ ነው፡፡” የናይጄሪያ ጦር ሰራዊት ስታፍ ኮሌጅ አባላት
· Visiting
Nigerian Military Delegation Visits EAII and Praises Ethiopia’s AI Solutions for Border Control, Smart Cities, and Crime Prevention
ከናይጄሪያ ጦር ሰራዊት ስታፍ ኮሌጅ የተውጣጡ ወታደራዊ ልዑካን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በኢንስቲትዩቱ ባዩት ስራ መደነቃቸውን ገልጸዋል። በተለይም ኢንስቲትዩቱ ለጉምሩክ ኮሚሽን ያለማው ስማርት የድንበር ቁጥጥር ስርዓት በገቢና ወጪ ንግድ ቁጥጥር ላይ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው አድንቀዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ኢንስቲትዩቱ ስማርት ከተሞችን በመገንባት እና ስማርት የፖሊስ ጣቢያዎችን በማቋቋም ወንጀልን ለመከላከል የሰራቸውን ስራዎች እንደ መልካም ተሞክሮ በመውሰድ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የጸጥታና ወንጀልን የመከላከል ተግባራቸውን ማዘመን እንዳለባቸው አብራርተዋል።
የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በአፍሪካ ቀዳሚ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ልማት ማዕከል የመሆን ራዕይ ይዞ እየሠራ ስለመሆኑ ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይወሰን ከአፍሪካውያን ወንድሞቹ ጋር በመተባበር ለአህጉሪቱ ዲጂታል ሉዓላዊነት መጠበቅ እንደሚተጋም ተናግረዋል።
የልዑካን ቡድኑ ከጉብኝቱ ጎን ለጎን በቀጣይ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute