የማላዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡
· Visiting
A senior delegation from Malawi explored Ethiopia’s AI achievements and discussed opportunities for future cooperation.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የዋና የዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊና የቴክኖሎጂ አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ዘርፎች እያከናወናቸው ያሉትን ስራዎች በተመለከተ ለጎብኝዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በገለጻቸውም ኢንስቲትዩቱ የኤአይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገራዊ የልማት ግቦችን የሚያሳኩ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን አስረድተዋል። ሁለቱ ሀገራት በዘርፉመስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። ጉብኝቱን አስመልክቶ የማላዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዑክ መሪ በጋራ
ፎስተር ሃራዋ ኢንስቲትዩቱ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ መሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ ዘርፎች ላይ በኢንስቲትዩቱ የተሰሩት ስራች ለአፍሪካ ለውጥ ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን በጉብኝታቸው ወቅት መገንዘባቸውን አስረድተዋል፡፡በቀጣይም በሀገራቱ መካከል ለሚኖረው የቴክኖሎጂ መስክ ትብብር ኢንስቲትዩት መነሻ መሆን የሚችል ተሞክሮ እንዳለው በማንሳት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute