“በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደምንሆን አንጠራጠርም” የአየር ኃይል ጥናትና ምርምር ማዕከል አባላት
· Visiting
Members of the Air Force Research and Development Center visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to learn about its AI research, applications, policy initiatives and capacity-building programs, while expressing interest in future technological collaboration.
የአየር ኃይል ጥናትና ምርምር ማዕከል አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች አማካሪ ሻምበል ይልማ (ዶ/ር)፤ ተቋሙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዙሪያ እያከናወናቸው ያሉ የምርምርና
ልማት ሥራዎችን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል። በገለጻቸውም ኢንስቲትዩቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸውን የተለያዩ መተግበሪያዎች ማልማቱን፣ የብሔራዊ የኤ.አይ ፖሊሲ ማዕቀፍ ማዘጋጀቱን እንዲሁም ወጣቶችን በክረምት (ሰመር) እና በቡት ካምፖች እያሰለጠነ መሆኑን ለጉብኝት ቡድኑ አብራርተዋል።
የአየር ኃይል ጥናትና ምርምር ማዕከል አባላት በኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሂደት የወደፊቷን ኢትዮጵያ እና ሀገራችን በኤ.አይ ያለችበትን ዕድገት ማየታቸውን ገልጸው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደምንሆን ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል። በቀጣይ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመሥራት ያላቸውን
ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute