በሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የተመራ የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት ጉብኝት አደርጓል፡፡
· Visiting
“የኤ.አይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሁሉም መስኮች ያሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል አቅም በኢንስቲትዩቱ እየተገነባ መሆኑን በጉብኝታችን ተረድተናል” የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሰላዲን ቶፊቅ፡፡
ለልኡካን ቡድኑ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በማብራሪያቸው ኢንስቲትዩቱ የፍትሕ ሥርዓቱን በኤ.አይ የተደገፈ ለማድረግ የሚያስችሉ ስርዓቶችን በማልማት ጥቅም ላይ እንዲውሉ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሰላዲን ቶፊቅ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መስክ ያስመዘገባቸው ስኬቶች እንዳስደነቃቸው እና ቴክኖሎጂውን በሁሉም ዘርፎች ለመጠቀም የሚያስችል አቅም በተቋሙ እንደተገነባ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህ ጉብኝትም የኤ.አይ ቴክኖሎጂን በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute