5ተኛ ዙር የኤ.አይ ሰመር ካምፕ 2026 የማስጀመሪያ መርኃ ግብር ተካሄደ
· Education
The fifth AI Summer Camp will equip 500 students with practical skills in AI, robotics, data science, and programming.
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ላለፉት ዓመታት ሲያካሂድ የነበረው የታዳጊዎች የክረምት ስልጠና ዘንድሮም በ500 ታዳጊዎች ስልጠና ጀምሯል፡፡ በመርኃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኤ.አይ የወደፊቱን ትዉልድ እና ሀገር የሚቀይር ነዉ ብለዋል። ይህንን ታሳቢ በማድረግ የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ በመገንባት ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል። ታዳጊዎች በሚኖራቸዉ የሁለት ወራት የስልጠና ቆይታ በርካታ ክህሎቶች የሚያዳብሩ በመሆኑ በትኩረት እና በትብብር እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የኢንስቲትዩት የስታርታፕ እና ኢንዱስትሪ ትስስር ዲቪዥን ኃላፊ ዮዲት ሞላ ለ5ተኛ ዙር የሚሰጠዉ ይህ ስልጠና ስለ መሰረታዊ ኤ.አይ ክህሎት፣ሮቦቲክስ፣ዳታ ሳይንስ፣ፕሮግራሚንግ እና ማሽን ለርኒንግ የካበተ ልምድ ባላቸዉ ከ50 በላይ የዘርፉ ባለሙያዎች በተግባር ታግዞ የሚሰጥ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።
ከማስጀመሪያው ስነ-ስርዓት ጎን ለጎን ሰልጣኞች እና ወላጆቻቸው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል። ይህ ስልጠና በኢትዮጵያ የዲጂታል ለውጥ ጉዞ ውስጥ የነገውን ትውልድ በዘመናዊ እውቀት ለመቅረጽ ትልቅ ሚና አለው፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute