"የራሳችን መረጃ ከሌለን የእኛ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ባዕድ ይሆናል" — ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)
· Other
Ethiopia Advances Data Sovereignty to Strengthen Digital Independence, AI Innovation, and Economic Competitiveness
''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት'' በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት መክፈቻዉን አድርጓል።
የኢትዮጵያአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለቀጣይ አስርት ዓመታት የሚዘልቅ አስተማማኝና ሉዓላዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት እየገነባች ትገኛለች። ዋና ዳይሬክተሩ እንደ ግብርና፣ ጤና፣ ፋይናንስ፣ ትምህርት እና ኢነርጂያሉ ቁልፍ የልማት ዘርፎች መረጃዎች በሀገር በቀል የክላውድ ቴክኖሎጂ እየተቀነባበሩ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ለሀገር በቀል አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስነ-ምህዳር መጎልበት ወሳኝ ግብዓት መሆኑን አብራርተዋል።
"የራሳችን መረጃ ከሌለን የእኛ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ባዕድ ይሆናል፤ የራሳችን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ከሌለን ደግሞ መረጃዎቻችን ይባክናሉ" በማለት የቴክኖሎጂ እና መረጃን መደጋገፍ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የመረጃክፍተቶችን ለመሙላት የተቀረጸው "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ብሔራዊ ስትራቴጂ፤ ሉዓላዊ የክላውድ ዳታ ማእከልን፣ ብሔራዊ የዳታ እንዲሁም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በትግርኛ እና በሶማሊኛቋንቋዎች የሰለጠነ ሀገር በቀል የትልቅ ቋንቋ ሞዴል (LLM) መገንባትን ያካተተ መሆኑን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያመረጃን ወደ አዲስ የኢኮኖሚ እሴት በመቀየር ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጥ ጠንካራ መሠረት እየገነባች መሆኑም በጉባኤው ተመላክቷል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute