በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የአየር ማረፊያዎች የተሳፋሪዎችን ቁጥር ለማስተዳደር እና ቅልጥፍናን ለማሻሻል ኤ.አይን እየተጠቀሙ እንደሆነ ተገለጸ።
· AI Solutions
Airports expand AI adoption to manage rising passenger traffic and improve operational efficiency.
የዓለማቀፍ የአየር ተሳፋሪዎች ቁጥር በ2026 10.2 ቢሊዮን ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም በየዓመቱ የ3.9 በመቶ ጭማሪ እንዳለው አልጀዚራ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህም ምክንያት የአየር ማረፊያዎች በመሠረተ ልማት እና በኤ.አይ ቴክኖሎጂ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እያደረጉ ነው ሲል ኤርፖርት ካዉንስል ኢንተርናሽናል ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
በተሳፋሪ ፍሰት አያያዝ፣ የጭነት መከታተያ፣ የጥገና ትንበያ፣ የሳይበር ደህንነት፣ የጠፉ እቃዎች አያያዝ እና የደንበኞች አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያስችሉ በኤ.አይ የታገዙ ሥርዓቶች በአውሮፕላን ማረፊያዎች የሥራ ሂደቶች ውስጥ እየተካተቱ ነው።
በኤ.አይ የተደገፉ የመረጃ ትንተናዎች አውሮፕላን ማረፊያዎች በፍተሻ፣ በኢሚግሬሽን እና በመሳፈሪያ ቦታዎች ላይ የሚፈጠረውን መጨናነቅ አስቀድሞ ለማወቅ ያስችላሉ። የባዮሜትሪክ መረጃዎችን ከኤ.አይ ጋር በማቀናጀት ፈጣን የኢሚግሬሽን አገልግሎት እና ቀልጣፋ የሻንጣ አያያዝ እንዲኖር በማገዝ ላይ ይገኛሉ።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute