የዓለም ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ፉክክር
· AI Investment
Amazon Invests $13 Billion in India to Expand AI Infrastructure and Accelerate Digital Economy Growth
የዓለም ታላላቅ የቴክኖሎጂ ተቋማት “ከኋላ መቅረት የለብንም” በሚል ፉክክር ውስጥ የገቡ ይመስላል። በዚህም ምክንያት በቅርብ ዓመታት በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በዘመናዊ የዳታ ማዕከላት መሠረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በከፍተኛ ፍጥነት እያለሙ ይገኛሉ።
ሮይተርስ በዘገባው አማዞን በሕንድ ያለውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የክላውድ መሠረተ ልማት ለማስፋፋት ተጨማሪ 13 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት
ሊያደርግ ነው።
ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት የአማዞን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዲ ጃሲ በኒው ዴልሂ ከሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ከተገናኙ በኋላ ይፋ የተደረገ ነው፡፡ በዋናነት በሙምባይና በሃይደራባድ ያሉ የዳታ ማዕከላትን አቅም ለማስፋፋት እንደሚውልም ተገልጿል።ይህ በሦስት ዓመታት ውስጥ አማዞን ለሕንድ ያደረገው ሦስተኛው ትልቁ ኢንቨስትመንት ነው።
ይህም ሕንድ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ለዳታ ማዕከላት ዋና ዓለም አቀፍ ማዕከል እየሆነች መምጣቷን ያሳያል። በተጨማሪም፣ የኤአይ ቴክኖሎጂ መስፋፋት ከፍተኛ የኮምፒውቲንግ አቅምና የዳታ ማዕከላት መሠረተ ልማት ፍላጎት እየፈጠረ ስለመሆኑ እና ሕንድም በዚህ ዘርፍ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እየሆነች መምጣቷን ያመለክታል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute