ኦፕን ኤ.አይ GPT-5.5 Instant የተሰኘ አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል ይፋ አደረገ፡፡
· AI Investment
enAI Launches GPT-5.5 Instant with Faster Performance, Reduced Hallucinations, and Advanced AI Productivity Capabilities
ኦፕን ኤ.አይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረውን GPT-5.5 Instant የተሰኘ አዲስ ሞዴል አስተዋውቋል። ይህ አዲስ ሞዴል
ቀደም ሲል የነበረውን GPT-5.3 Instantን ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሲሆን በተለይም እንደ ሕግ፣ ህክምና እና ፋይናንስ ባሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሹ ዘርፎች ላይ የሚታየውን ያልተረጋገጠ መረጃ የመፍጠር ወይም የ"Hallucination" ችግር በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀርፍ ነው።
አዲሱ ሞዴል የቀድሞውን ፈጣን ምላሽ የመስጠት ብቃት እንደጠበቀ የሚቆይ ከመሆኑም በላይ በሶፍትዌር ማበልፀግ እና በእውቀት ላይ በተመሰረቱ ስራዎች ላይ መሻሻል ማሳየቱን ኩባንያው አረጋግጧል። በተጨማሪም ሞዴሉ መረጃን በማስታወስና ካለፈው ሁኔታ ጋር በማዛመድ ረገድ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተገነባ በመሆኑ የግል ንግግሮችን፣ ፋይሎችን እና ጂሜይልን በማጣቀስ ለእያንዳንዱ ተጠቃሚ የተለየና የተቀናጀ ምላሽ የመስጠት አቅም አለው።
በአሁኑ ወቅት ለክፍያ ተጠቃሚዎች በድረ-ገጽ የቀረበ ሲሆን፣ በቀጣይ ሳምንታት ለነፃ ተጠቃሚዎች እና በሞባይል መተግበሪያ ላይ ይለቀቃል። ቻትጂፒቲ መረጃውን ከየት እንዳመጣው ለተጠቃሚው የሚያሳይበት አዲስ ግልጽነት ያለው አሰራር ተጨምሮበታል ሲል ቴክ ክራንች ዘግቧል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute