ጣሊያን ለአፍሪካ የኤአይ መሠረተ ልማት መጠናከር የገንዘብ ድጋፍ አቀረበች፤ ኢትዮጵያም የዚህ ማዕቀፍ አካል ናት
· Other
Italy’s Mattei Plan Supports Ethiopia and 13 Other African Countries in Strengthening AI Capacity and Digital Infrastructure.
ጣሊያን በ14 የአፍሪካ ሀገራት የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል መሠረተ ልማትን ለማጠናከር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቷ ተገለጸ። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያ፣ አልጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ሞዛምቢክ እና ጋና የዚህ ድጋፍ ተጠቃሚ ከሆኑ 14 ሀገሮች መካከል ይጠቀሳሉ።
በጣሊያን መንግሥት እና በዓለምአቀፍ ተቋማት ትብብር የሚከናወነው ይህ የ“ማቴኢ ፕላን” (Mattei Plan) አካል የሆነው ተግባር በአፍሪካ የኤአይ አቅምን በማሳደግ ሀገራቱ በፈጣን ለውጥ ላይ ካለው የቴክኖሎጂ ኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው።
ይህ የጣሊያን ድጋፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ14ቱ የአፍሪካ ሀገራትየዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን ለማጎልበት፣ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማትን ለማስፋፋት እና ሀገራቱ በኤአይ ዘርፍ የራሳቸውን ሉዓላዊ አቅም እንዲገነቡ የሚያግዝ መሆኑ ታውቋል። በተለይም አፍሪካ በኤአይ ቴክኖሎጂ ከውጭ አቅራቢዎች ብቻ ጥገኛ እንዳትሆን የአህጉሩን የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ የድጋፉ ዋነኛ ዓላማ ነው።
ኢትዮጵያ ከጣሊያን ጋር አጋርነት ካላቸው 14 አፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን፤ በሰፊው እየተተገበረ ባለው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂዋ መሠረት የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ማዕከል ለመሆን ወሳኝ ርምጃዎችን እየወሰደች ነው።
ድጋፉ አፍሪካ በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በፋይናንስ ዘርፎች የራሷን የኤአይ መፍትሔዎች እንዲኖራት የሚደረገው ጥረት ከኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት ግቦች ጋር በቀጥታ የሚጣጣም ነው። ይህ ድጋፍ ሀገራችን እየተገበረች ያለውን የዲጂታል ሽግግር ጉዞ ለማፋጠን እና የቴክኖሎጂ አቅሟን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute