የፓን አፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርታፕ ቡትካምፕ ፕሮግራም (Pan-African AI Ventures Residency) ማስጀመሪያ መርኃግብር ተካሄደ፡፡
· Education
AI UniPod Programme Launches with 51 Innovators from 12 African Countries to Advance Inclusive AI Solutions
በማስጀመሪያ መርሓ ግብሩ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከአርቲፊሻል
ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለመሆን ተቋም ከማቋቋም ጀምሮ ብሄራዊ የኤ.አይ ፖሊሲ እና ዲጂታል ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ የሀገሪቱን ተጠቃሚነት
ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ለዚህ ማሳያ አንዱ የኤ.አይ ዩኒፖድ መሆኑን በማንሳት ለአፍሪካ አህጉር በአጠቃላይ የሚጠቅም እሴት ለመፍጠር፣ እውቀትን፣ ተሞክሮንና ፈጠራን በአህጉሪቱ ሀገራት መካከል ለማጋራትም በማለም እንደተቋቋመ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ተባባሪ የሆኑ አጋር አካላትን አመስግነዋል፡፡
በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪን በበኩላቸው የጃፓን መንግስት በሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኩል በየዓመቱ የ1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በመላው አፍሪካ ለሚገኙ የኤ.አይ ዩኒፖዶች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል:: የጃፓን መንግስት ይህንን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል
አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡
የዩ.ኤን.ዲ.ፒ የአፍሪካ ቀጣናዊ አገልግሎት ማዕከል ዳይሬክተር ማቲያስ ዛና ናብ(ዶ/ር) እንደገለጹት በአፍሪካ የሚደረገው የኤ.አይ ልማት እና ትግበራ አካታች
እና ፍትሀዊ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑን በመርሓ ግብሩ አንስተዋል፡፡
ለተመረጡት የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች በሚኖራቸው ቆይታ እርስ በእርስ እንዲደጋገፉ እና ያገኙትን ዕድል በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ዩ.ኤን.ዲ.ፒ፣ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ እና የጃፓን የኢኮኖሚ፣ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር(METI) ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡ ከአስራ ሁለት የአፍሪካ ሀገራት የተመረጡ 51 የኤአይ ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች በፕሮግራሙ ይሳተፋሉ፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute