‘’በኢንስቲትዩቱ ስታርታፕ ማዕከል ያሉ የፈጠራ ሀሳቦች ለኛ ድርጅትም የሚጠቅሙ ሆነው አግኝተናቸዋል፡፡’’ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ
· Visiting
Ethiopost executives explore AI-driven innovations and discuss potential collaboration with the Institute.
የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ኢንስቲትዩቱ ኤ.አይን በተለያዩ ዘርፎች ለችግር ፈቺነት እንዴት እያዋለ እንደሆነ ለኃላፊዎቹ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ጉብኝቱ ከዚህ በፊት ስለኢንስቲትዩቱ የነበራቸውን ግንዛቤ ይበልጥ ያጠናከረ እና የሚያስገርሙ ጉዳዮችን የተመለከቱበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎችም ዘርፎች የሰራቸው ስራዎች ለሌሎች ሀገሮችም ምሳሌ መሆን የሚችሉ ናቸው ብለዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በኢንስቲትዩቱ የኤ.አይ የስታርታፕ ማዕከል በኤ.አይ በመታገዝ ለሀገርና ለብዙ ተቋማት የሚጠቅሙ በርካታ ፈጠራዎችን ማየታቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ለኢትዮጵያ ፖስታ የሚጠቅሙ ሆነው ካገኟቸው የስታርታፕ ፈጠራዎች ጋርም በቀጣይ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute