በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥነ ምህዳርን ማስፋት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እንደሚከናወኑ ተገለፀ፡፡
· Other
EAII Outlines Strategic Initiatives to Strengthen Ethiopia’s AI Ecosystem and Digital Services
ይህ የተገለፀው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን በይፋ ባስጀመሩበት መድረክ ላይ ነው፡፡
በመርኃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እንደገለፁት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥነ ምህዳርን ማስፋት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም ሀገራዊ የክላውድ አቅምን ከመጠቀም ባሻገር ውጤታማ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር እንደሚደረግ ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል። በዚህም በተደራጀ አግባብ መረጃዎች ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲውሉ የሚሰራ ሲሆን፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ገለልተኛ ብሔራዊ የመረጃ ባለስልጣን ወደ ስራ እንዲገባ ይደረጋል።
ዲጂታል የአገልግሎት አሰጣጦችን የማናበብና ወጥ የማድረግ ስራ ደግሞ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሌላኛው ትኩረት የሚደረግበት ጉዳይ መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute