በአንድ መድረክ ላይ 110 ሰው መሰል ሮቦቶች አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዝገቡ
· Other
AGIBOT’s 110 Humanoid Robots Set Guinness World Record with Synchronized Dance
በAGIBOT የተሰሩት110 የA3 ሰው መሰል ሮቦቶች በአንድ ላይ የተቀናጀ የዳንስ ትርኢት በማቅረብ በአንድ ጊዜ የዳንስ እንቅስቃሴ ያቀረቡ፤ ከሁሉም በላይ
ብዛት ያላቸው ሰው መሰል ሮቦቶች በሚል የጊነስ ክብረወሰን እውቅና አግኝተዋል።
ይህ ትርኢት በርካታ ሮቦቶችን በአንድ ጊዜ በትክክል ማስተባበር የሚችለውን የቴክኖሎጂ አቅም ያሳየ ነው።ሮቦቶቹ በሴንቲሜትር ደረጃ ትክክለኛ የቦታ መለያ
ቴክኖሎጂ (UWB) እና LinkBots በተሰኘው የበርካታ ሮቦቶች ቁጥጥርና ማስተባበሪያ ስርዓት በመታገዝ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በትክክል አከናውነዋል።
ትርኢቱንም ያለምንም ስህተት ማጠናቀቃቸው በቴክኖሎጂው የተገኘውን ከፍተኛ የቅንጅት አቅም ያሳያል።
የሰው መሰል ሮቦቶች በተናጠል ከሚያከናውኑት ተግባር ባለፈ በቡድን ተደራጅተው ውስብስብ ሥራዎችን በትክክል ማከናወን ወደሚችሉበት አዲስ የሮቦቲክስ ዘመን መገባቱን የሚያመለክት ሌላ ትልቅ ምዕራፍ ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute