"አፍሪካዊያን ተመራማሪዎች ለአህጉሪቱ ምን ያህል አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችሉ የተመለከትንበት ጉብኝት ነው" የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀሲካ አሉፖ
· Visiting
Uganda’s Vice President Visits EAII and Calls for Stronger African Cooperation in AI Development
በኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀሲካ አሉፖ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ይፋዊ ጉብኝት አካሂዷል።
ምክትል ፕሬዝዳንቷ ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ኢትዮጵያ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ትምህርትና ሥልጠና በፍጥነት ከማስፋፋት ባሻገር ቴክኖሎጂውን በተግባር በመጠቀም ረገድ ያስመዘገበችዉን ዉጤት መገንዘባቸዉን አስታዉቀዋል።
የኢንስቲትኡቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለልኡክ ቡድኑ ባቀረቡት ገለፃ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ስኬታማ ስራ ለአፍሪካዉያን እህት ወንድሞች ለማጋራት ያላትን ቁርጠኝነት አስረድተዋል። ኡጋንዳ የኤ.አይ ፖሊሲና ሕጋዊ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ላይ ትገኛለች ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቷ ይህ ጉብኝት ከኢትዮጵያ ልምድ ለመቅሰም እንደሚያግዛቸዉ ገልፀዋል።
በኢንስቲትዩቱ በነበራቸዉ ጉብኝት አፍሪካዊያን ተመራማሪዎች ለሀገራቸዉ ብሎም ለአህጉራችን አፍሪካ ምን ያህል አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኙ መመልከታቸዉን ገልጸዋል። የኤ.አይ ቴክኖሎጂን መጠቀም እና ማልማት ያልጀመሩ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ወደ ኢንስቲትዩቱ በመምጣት ልምድ እንዲቀስሙና የተከናወኑ ሥራዎችን እንደ አብነት እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል። አክለዉም ሀገራቱ ያላቸዉን ፈጠራ፣ክህሎት እና ልምድ በመጋራት በትብብር መስራት እንደሚገባም ምክትል ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸዉ አንስተዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute