የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የቴክኖሎጂ ትብብር ማጠናከሪያ ጉብኝት::
· Visiting
Russian Ambassador to Ethiopia Evgeny Terikhin visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute to discuss cooperation in artificial intelligence, research and development, human resource development, and technology transfer.
በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ በሀገሪቱ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ እያከናወናቸው ያሉ ወሳኝ ስራዎችን አስመልክተው ለ አምባሳደሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ የሚያከናውናቸው የምርምርና ልማት ስራዎች በኢትዮጵያ ቅድሚያ በተሰጣቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ እምርታ እንዲመዘገብ ማስቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ትብብር እና የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት አውስተው በምርምርና ልማት፣ በሰው ሃይል ልማት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ኢትዮጵያ እና ሩስያ በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ይህ የሁለቱ ሀገራት አጋርነት የብሪክስ አባል ሀገራት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ለጋራ ዕድገትና ተጠቃሚነት ለማዋል ከሚያደርጉት ሰፊ ጥረት ጋር የሚጣጣም ነው።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute