አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በዩናይትድ ኪንግደም ከ500 ሚልዮን ፓዉንድ በላይ ከምዝበራ ማዳን አስቻለ።
· Robotics
ዩናይትድ ኪንግደም የሀብት ምዝበራን ለመቆጣጠር ፍራዉድ ሪስክ አሰስመንት አክስለሬተር የተባለ የኤ.አይ ሥርዓት ትጠቀማለች። በዚህም በአንድ አመት ብቻ 500 ሚልዮን ፓዉንድ በላይ ማዳን መቻሉ ተዘግቧል።
ቢ.ቢ.ሲ ባወጣዉ ዘገባ እንደተገለጸዉ ከመጭበርበር የዳነው ሀብት ከታለመላቸዉ ዓላማ ዉጪ የዋሉ፣ በሀሰተኛ ተቋማት እና ግለሰቦች ስም የተጭበረበሩ ገንዘቦች የተካተቱበት ነዉ። በሥርዓቱ አማካኝነት በርካታ ተቋማት ከመንግሥት የወሰዱትን ብድር ሳይከፍሉ ለመሰወር ሲሞክሩ ማስቆም መቻሉ ተገልጿል።
የኤ.አይ ሥርዓቱ አዳዲስ ፖሊሲዎች በሚወጡበት ጊዜ ያሉበትን ዉስንነቶች በመተንተን አፈጻጸማቸዉ ላይ የሚፈጠር ክፍተትን አስቀድሞ መተንበይ እንደሚያስችል ተነግሯል።
የህዝብ እና መንግስት ሀብት ብክነትን ለመከላከል ያስቻለዉን ሥርዓት መጠቀም የሚፈልጉ ሀገራት ካሉ በዓለማቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚቻልበት አሰራር ለመዘርጋት ዩናይትድ ኪንግደም ፈቃደኛ መሆኗን አስታዉቃለች።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute