ዩቲዩብ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አገልግሎቱን ወደ ስማርት ቴሌቪዥኖች አስፋፋ፡፡
· AI Investment
YouTube tests AI assistant on smart TVs, enabling real-time video explanations and enhanced viewing quality.
ዩቲዩብ ተመልካቾችስለሚመለከቱት ቪዲዮ ጥያቄ ቢኖራቸው ቪዲዮውን መዝጋት ሳይጠበቅባቸው ማብራሪያ እንዲጠይቁ የሚያስችል የኤ.አይ የውይይት ረዳት (Conversational AI) ሥርዓት በስማርት ቴሌቪዥን መተግበሪያዎቹላይመሞከር መጀመሩን አስታወቀ።
ከዚህ ቀደም በሞባይል እና በድረ-ገጽ ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረው ይህ አገልግሎት አሁን ተመልካቾች የሚመለከቱትን ቪዲዮ ሳይለቁ ስለይዘቱ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ ያስችላቸዋል። ተጠቃሚዎች በቴሌቪዥንገጻቸው ላይ ያለውን “Ask” የሚል ምልክት በመጫን የኤ.አይ ረዳት ማግኘት ይችላሉ።
አገልግሎቱ ከጥያቄና መልስ በተጨማሪ ዝቅተኛ ጥራት ያላቸውን ቪዲዮዎች በኤ.አይ አማካኝነት ወደ ተሻለ የጥራት ደረጃ የሚያሳድግ አዲስ ቴክኖሎጂ እንደሆነ ዩቲዩብ አስታውቋል።
ተጠቃሚዎችየቴሌቪዥን ሪሞታቸውን በመጠቀም ስለቪዲዮውይዘት፣ ስለምግብ አሰራር ግብዓቶች ወይም ስለዘፈን ግጥም ትርጉም ወይም ማብራሪያ መጠየቅና ፈጣን ምላሽ ለማግኘት ያስችላቸዋል።
ለቲቪ እና የስትሪሚንግ አገልግሎቶች የታዳሚ መጠንን ሪፖርት በማድረግ የሚታወቀውየኒልሰን ሪፖርት የ2025 (እ.ኤ.አ) መግለጫ እንደሚያሳየውዩቲዩብ ከጠቅላላ የቴሌቪዥን ታዳሚዎች 12.4% ድርሻ ይይዛል፡፡ ይህም እንደ ዲዝኒ እና ኔትፍሊክስካሉዋናዋናየዘርፉ አገልግሎት አቅራቢዎች መብለጡን አመላክቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute