የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
· Visiting
Advancing National Development Through AI-Driven Digital Systems
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) አዲሱን የኢንስቲትዩቱን ዋና መሥሪያ ቤት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱ ለመጪዉ ትዉልድ የሚተላለፍ አቅም የተፈጠረበት መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸዉ የቴክኖሎጂዉ ቀዳሚ ተጠቃሚ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ፍፁም ከኢንስትቲዩቱ ጋር የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸዉንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር አበልጽጎ የሰጠዉ ዲጂታል የእቅድ እና ሪፖርት መከታተያ ሥርዓት አሰራርን ከማዘመን አልፎ ዉጤታማነትን መጨመሩንም አክለዋል። ይህም ኢንስቲትዩቱ አሰራሮችን በማዘመን ለሀገር እድገት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute